Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
157K subscribers
7.87K photos
365 videos
70 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ከ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። የዛሬው ውይይታችን በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደን ሆኗል። በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮቻችንን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተናል።

Ahead of the 17th BRICS Summit in Rio de Janeiro, I had the pleasure of meeting with President Luiz Inácio Lula da Silva to discuss bilateral and multilateral issues. Our meeting today marks another step forward in strengthening the relationship between our two nations, which has grown significantly in recent years. We agreed to further enhance trade and investment ties across various sectors.
ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል።

Thank you, Premier Li Qiang, for our engaging exchange this morning on Ethio-China relations, now in its 55th year. As all-weather partners, our cooperation has borne significant fruit over the past seven years. By maintaining our focus on key economic pillars, including industry, mining, and ICT, we see even greater potential to deepen collaboration and build capabilities in these areas, as well as in artificial intelligence, logistics, and the clean energy sector.
ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል። የበለጠ እኩልነት እና ፍትኅ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን። የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል።

Alongside fellow BRICS leaders at this year’s summit in Rio Di Janeiro. Together, we continue to strengthen our partnership in pursuit of a more equitable and just, world. The BRICS platform remains vital in advancing shared development and global cooperation.
በመትከል ማንሰራራት: ዛሬ ማለዳ የችግኝ ተከላ መርሃግብራችንን በመቀጠል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሂደናል።

Renewal through Planting: This morning, we continued our planting initiative alongside staff members of the Office of the Prime Minister.