Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
158K subscribers
8.06K photos
374 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ዛሬ በመቀጠሉ ደስ ብሎኛል። እነዚህ ውይይቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅርበት አብረው እንዲሠሩ፣ ለወቅታዊ ጉዳዮች የጋራ መፍትሔ እንዲያበጁ፣ እንዲሁም ለሀገራችን እና ለሕዝባችን የሚጠቅም የዕድገት እና የብልጽግና የጋራ ራእይን እንዲያዘጋጁ ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው።

I am pleased to witness the continuation of the political dialogue platform with another session taking place today. These discussions are key in enabling political parties to work closely together; jointly address issues that arise and co-create a vision of growth and prosperity in service to country and our people.
ከአማራ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የክልል መስተዳድሮች እንዲሁም ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ ውይይት አካሂደናል። ያሉትን ችግሮች ፈትሸን፣ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል::

Bulchitoota naannolee Amaaraafi Beenishaangul Gumuz akkasumas qaamolee nageenyaa waliin taanee walitti bu'iinsa Matakkalitti uumame irratti marii'anneerra. Rakkoolee jiran sakattaanee, naannichatti nageenya waaraa buusuuf kallattiiwwan keenyeerra.

We held discussions with the regional administrations and security sector of both Amhara and Benishangul Gumuz regions on recent conflict that occurred in Metekel. Our lengthy discussions examined the challenges for which we have set directions to ensure sustainable peace in the area.
ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር፣ የአንበጣ መንጋ ጥቃትን ስለመከላከልና ተያያዥ ተፅዕኖዎች እና ስለ አፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ የሰላም እና መረጋጋት ጉዳዮች አስመልክቶ ጥሩ የስልክ ውይይት አካሂደናል።

Barreessaa Olaanaa Mootummoota Gamtoomanii, Antooniyoo Guutereez waliin weerara awwannisaa ittisuuf tattaaffii taasifamu cimsuufi dhiibbaa weeraarichaan walqabatee uumamu ilaalchisee, akkasumas dhimma nageenyaafi tasgabbii naannoo Gaanfa Afrikaa irratti bilbilaan marii gaarii gooneerra.

Good phone call with Secretary-General of the United Nations, António Guterres on strengthening the effort of the locust invasion and its aftermath effects and We have also discussed on the Horn of Africa’s regional peace and security issues.
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርነትን ተረክበው መንቀሳቀስ ከጀመሩ አንስቶ ፤ የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ እያደረጉት ላለው ጥረት ዛሬ በነበረን የስልክ ውይይት አድናቆቴን ገልጫለሁ። በተጨማሪም የሀገሮቻችንን ሁለትዮሽ ግኑኝነቶች እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም ፍሬያማ ምክክር አድርገናል።

Pirezdaantiin Afrikaa Kibbaa Siiriil Raamafoosaa edda dura taa'aa Gamtaa Afrikaa ta'anii hojii eegalanii carraaqqii cimaa dhimmoonni Afrikaa, Afrikaanotaan akka furmaata argatan godhaniif har'a bilbilaan dinqisiifannaakoo ibseeraafi. Kana malees walta'insa garlamee biyyoota keenya lachaniifi dhimmoota naannwaa ardichaarratti marii gaarii gooneerra.

In our Phone conversation with the South African President Cyril Ramaphosa today, I have appreciated his guidance as AU Chairperson and individual great effort in ensuring a trend of resolving African cases by Africans. We have also discussed about the mutual cooperation between our two countries and the overall sub regional issues.
ወንፊት ማበጠሪያ እንጂ አበጣሪ አይደለም ፡፡ መንቀል ከማንቀልቀል በእጅጉ ይለያያል፡፡ ዓሣን ስለ ደን ሕይወት እንደማንጠይቅ ሁሉ ድመትንም ስለ ጥልቁ ባሕር ኑሮ አስረጂን አንላትም፡፡ የእንጨት ሙቀጫና የሸክላ ድስት በጥንካሬ ይለያያሉ ፡፡ ሙቀጫን በትር አይሠብረውም ፡፡ እሳት ግን ወደ አመድነት ይቀይረዋል ፡፡ ሸክላ ድስት በእሳት አይነድም ፡፡ በትር ግን ያነካክተዋል ፡፡ በሸክላ ድስት ገብስ እንወቅጣለን ብለን ብንነሳ ሸክላው ፍርክስክሱ እንደሚወጣ ሁሉ እሳት የገባ የእንጨት ሙቀጫ ነዶ ከሠልና ዐመድ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ምክንያትና ውጤትን፣ ወቅትና ቦታን፣ አድራጊና ተደራጊን፣ ጥንካሬና ድክመትን በትክክል ለይቶ ማወቅ ለማወቅም ጥረት ማድረግ የዕውቀትና ጥበብ መንገድ ነው ፡፡ በዕውቀት እርከን ውስጥ ማስተዋል የበኩር ልጅ፣ ስሌት ሁለተኛ፣ ጥበብ ሦስተኛ ልጆች ናቸው፡፡
የመደመር መንገዳችን ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቻችን የተዘረጋ አዲስ የብርሃን መንገድ ነው፡፡ መዳረሻ ግባችን ብልጽግና ነው። ብልጽግና ንጋት እንጂ ሌት ሆኖ ማንንም አይጋርድም፣ አይሸፍንምም፡፡ በትኅትና የማይበርድ ቁጣ፣ በልግስና የማይጠወልግ ስስት፣ በደግነት የማይሰበር ክፉት፣ በመደመር የማይጠገን ልዩነት፣ በብልጽግና የማይኮሰምን እርዛት፣ በሐቅ የማይረታ ሐሰት አለመኖሩን ዐውቀን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለን፡፡
በራሳችን ዘመን ደረጃ የምንመዘን ትውልዶች ነን፡፡ ለሀገራችን ባስቀመጥነው ጡብ፣ ለኢትዮጵያ በከፈልነው መስሥዋትነት፣ ለሕዝባችን በዋልነው ውለታ ልክ እንዳኛለን። አዲስ ታሪክ ሠሪዎች ጭምር እንጂ፤ ነባር ታሪክ ተራኪዎች ብቻ አይደለንም፡፡ በራሳችን ሐሳብ ተነጋግረን የምንግባባ እንጂ፤ እየተወዛገብን ዕንቁ ዘመናችንን በከንቱ አናባክንም። የእኛ ትውልድ በሀገራችን ታሪክ ወርቃማው ትውልድ ሆኖ ያልፋል።
ዩኒቨርስቲዎቻችንን መልሶ ለመክፈት የምንዘጋጅበት ወቅት ነው። በዚህ ረገድ ዛሬ ከሰዓት በሀገራችን የሚገኙ የሁሉንም ዩኒቨርስቲዎች አመራሮች እና የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን አመራሮች አግኝቼ ውይይት አካሂደናል። ኮቪድ19ን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል የሚደረገውን ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ቃኝተናል። በተጨማሪም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምንም ዓይነት የሰላም እና የጸጥታ ችግር እንዳይገጥም ለማድረግ ፤ ቢገጥምም ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ ባላቸው ዝግጁነት ላይ ተወያይተናል። ዩኒቨርስቲዎች የዕውቀት እና የፈጠራ ማዕከላት እንደ መሆናቸው፣ አመራሮች ለትምህርት እንዲሁም ለቱሪዝም የሚሆንን ነባራዊ ሁኔታ እንዲያመቻቹ ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጠናል።

Yunivarsiitiiwwan keenya deebisnee banuuf qophiirra wayita jirru kanatti, har'a waaree booda hooggantoota yunivarsiitiiwwan biyya keenyaa hundaafi kan Ministeera Saayinsiifi Barnoota Olaanaa waliin walargee marii gooneerra. Haala ofeeggannoo ittisa #COVID-19 hojiirra oolchuun, adeemsa baruufi barsiisuu itti fufsiisuuf qophii taasifamuufi dhimmoota kanaan walqabatan ilaalleerra. Kana malees dhaabbilee barnoota olaanaa rakkoon nageenyaafi tasgabbii akka isaan hin mudanne gochuuf, akkasumas yoo mudatee argamee hatattamaan akka furamu gochuuf qophii qabanirrat
ሀገር መውደድ ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን ለብልጽግናዋ መትጋት ነው ፡፡ ማንም ሌት የሚተኛው ቀን ባነጠፈው መደብ ነው፡፡ ያለዛሬ መሥዋዕትነት ያማረና የሠመረ ነገ አይገኝም። ከትናንት እንማራለን፤ ዛሬ ላይ እንሠራለን፤ ነገን የተሻለ እናደርጋለን። ብልጽግና ይህን መንገድ መርጦ በመከተሉ ክብሬ ታላቅ ነው፡፡

Biyya jaalachuu jechuun waan kanbiraa utuu hin ta'iin badhaadhinasheetiif jabaatanii hojjechuidha. Namni kamiyyuu halkan kan rafu siree guyyaa aferradha. Aarsaa har'aa malee waan bareedeefi milkaa'e hin argamu. Kaleessarraa ni baranna, har'a ni hojjenna, bor kan wayyu ni taasifna. Badhaadhinni daandii kana filatee hordofuusaatiif ulfina guddaan qabaafi.
የጊዜ ጉዳይ እንጂ እሳት የሚቆሰቁስ እንጨት ራሱ መንደዱ አይቀርም። በፖለቲካም ሆነ በሌላ ዘርፍ የሚኖረው አካሄድ ከንግግር ይልቅ ኃይልን፣ ከስክነት ይልቅ ሁከትን፣ ከመግባባት ይልቅ ጠብ አጫሪነትን የሚያስቀድም ከሆነ፣ እንዲህ ዓይነት መንገድ ቀስ በቀስ ባለቤቱን ይዞ እንደሚጠፋ ግልጽ ነው። ብልጽግና የሠላምና የመደመር ውጤት እንጂ፤ በጦርነትና በውድመት የሚሳካ አይደለም።

Yeroof malee mukni qoraanii ibbidda tuttuqatu ofiisaa boba'uunsaa hin oolu. Adeemsi gama siyaasaatiinis ta'e kanbiraatiin deemamu mariirra humna, tasgabbaa'uurra hookkora, waliigaluurra lola kaasuuf kan dursa kennu yoo ta'e, daandichi suuta suuta abbicha fudhatee akka badu ifadha. Badhaadhinni bu'aa nagaafi ida'amuuti malee, waraanaafi barbadeessuudhaan kan galma gahu miti.
በዛሬው የማክሮ-ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባ፣ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከውጪ ንግድ የተገኘውን ገቢ፣ የዋጋ ግሽበት እና ተያያዥ ርምጃዎች፣ የመንግሥት ገቢ እና የሥራ ክንውን ሁኔታን ገምግመናል። ለያዝነው ዓመት በለየናቸው ዐበይት ቀዳሚ ጉዳዮች መሠረት፣ ኮሚቴው ለቀጣይ ሩብ ዓመት የሚሆኑ ግቦችን ለይቶ ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጧል።

Walgahii Koree Dinagdee Maakroo har'aatiin kurmaana waggaa jalqabaatti: galii alergiirraa argame, tarkaanfii qaala'uu gatii tasgabbeessuuf fudhatamee, galii mootummaa argameefi raawwii hojii gamaaggamneerra. Tartiiba duraaduubaa ijoo bara kanaaf kaa'amanirratti hundaa'udhaanis, Korichi kurmaana waggaa iiti aanuuf galmawwaniifi kallattii kaa'eera.

In today’s macro-economic committee meeting, we have evaluated performance of first quarter export earnings, inflation response measures, government revenue and jobs performance. Based on key priorities set for the current year, the committee has put in place targets and set a direction for the next quarter.