Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
158K subscribers
8.06K photos
375 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
በዚህ ፈታኝ ወቅት አጋሮቻችን ወሳኝ የድጋፍ ምንጭ ሆነውናል። አብሮ የመቆምን ጠቀሜታም በተጨባጭ ተመልክተናል። ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር የነበረኝ የስልክ ውይይት ያረጋገጠልኝ ይህንኑ ነው። ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን እና ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገልጸውልኛል።

Yeroo rakkisaa kana keessatti faayidaa waliin dhaabachuu arguuf akka dandeenyetti, michuuwwan keenya yeroo balaa #COVID-19 kana keessa gahee ijoo ta'e bahaa jiru. Ministira Muummee Noorwey, Ernaa Soolbergi waliin marii gaarii bilbilaan gooneen biyyi isaanii #Itoophiyaa waliin dhaabachuufi deeggarsa gootu kan itti fuftu ta'uu naa ibsaniiru.

Our partners have been key to us during the #COVID19 crisis as we have witnessed the importance of standing together in trying times. Fruitful phone call with Prime Minister Erna Solberg on #Norway’s continued solidarity and support to #Ethiopia.
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በብዙ የተፈጥሮ እና የባህል መስህቦች የታደለ ነው። እነዚህን መልካም ጎኖች ለመጠቀም በጋራ ከሠራን፣ ክልሉ ለሌሎች የሚተርፍ የልማት ማዕከል እንደሚሆን ለበርካታ ጊዜያት ተናግሬያለሁ።

ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ ወደ ክልሉ በተደጋጋሚ በመጓዝ ለማኅበረሰብ ልማት በእጅጉ ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ከአንደበታቸው አድምጫለሁ። ሁሉንም መሠረታዊ ፍላጎቶች በአንድ ጊዜ ለማሟላት የሚቻል ባይሆንም፣ በዚህ ወቅት ዐበይት የመሠረተ ልማት፣ የኢንቨስትመንት እና ተያያዥ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ዛሬ ከክልሉ የዞን አመራሮች ጋር በነበረን ውይይት፣ በደቡብ ክልል ባለ ብዙ ገጽ ዕድገት እና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የአስተዳደራዊ መዋቅር መርኆውን ቅድሚያ ሰጥቶ መመልከት አስፈላጊ እንደ ሆነ ተስማምተናል። በዚህ ውይይት፣ በዝርዝር ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ጉዳዮችም ተነሥተዋል። ጉዳዮቹ የበለጠ ዳብረው ተመልሰን እንድንወያይባቸው ስምምነት ላይ ደርሰናል።

Naannoon Sabaafi Sablammoota Kibbaa hawwattoota uumamaafi aadaatiin kan dhangi'amedha. Cimina kanatti fayyadamuuf waliin yoo hojjenne, naannichi wiirtuu misoomaa kanbiroof irraa hafuu danda'u akka ta'u yeroo mara kaaseera.

Waggoota lamaan darbanitti gara naannichaa irra deddeebi'ee dhaquudhaan dhimmoota misooma hawaasaatiif baay'ee barbaachisan afaan isaaaniirraa dhaggeeffadheera. Fedhiiwwan bu'uraa hunda al tokkotti guutuudhaaf kan hin danda'amne ta'us, yeroo kanatti hojileen ijoo misooma bu'uraa, invastimeentiifi isaan walqabatan hojjetamaniiru.

Marii har'a hoogantoota godinaalee naannichaa waliin gooneen, Naannoo Kibbaatti guddinni fuula danuu qabuufi nagaan akka jiraatu, qajeeltoo caasaa bulchiinsa dursa kenninee ilaaluun barbaachisaa akka ta'e waliigalleerra. Marii kana irratti dhimmoonni kanbiroon gadifageenyaan ilaalamuu qabanis ka'aniiru. Dhimmoonni kunneen caalaatti gabbatanii deebinee irratti marii'achuuf waliigalleerra.

I have shared many times that the Southern region is bestowed with many natural and cultural endowments that position it as a pillar of national multi sectoral development if we work together to harness this strength.

Over the past two years, I have traveled extensively within the region to listen from the people on what they consider crucial to the development of their communities. While it remains that not all needs can be fulfilled in a short period of time, we have also marked key milestones in addressing some of the infrastructure, investment and other related needs within this period.

In my discussion today with the zonal leadership of the region, we have asserted the primacy of addressing the organizing principle within the region that will best respond to the multidimensional growth and sustainable peace of the Southern people. During this discussion, additional issues that need to be further refined have been identified and agreement reached to return and deliberate after further refining proposed ideas.

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
ባለፈው ዓመት የ #አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት የሕዝቡ ምላሽ ከሚጠበቀው በላይ አዎንታዊ እና አስደናቂ ነበር፡፡ 4 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል አቅደን ፈጽመነዋል፡፡ በዚህ ዓመት ደግሞ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ይዘናል፡፡ ትልቅ ሕልም እናልማለን፤ የላቀ ግብ እናሳካለን፡፡ የጀመርነውን እስከ ፍጻሜ እናደርሳለንልቀት፡፡ ሁላችን እንነሣለን፤ ኢትዮጵያንም አረንጓዴ እናለብሳለን። እንደሚሳካልንም እምነቴ ነው፡፡

Bara darbe yeroo biqiltuu dhaabbii #AshaaraaMagariisa deebiin uummataa kan eegamee olitti gaariifi dinqisiisaa ture. Biqiltuuwwan biliyoona 4 dhaabuuf karoorfannee raawwanneerra. Bara kanammoo biqiltuuwwan biliyoona 5 dhaabuuf karoorfanneerra. Guddifnee abjoonnee galma olaanaaf yaaduun murteessaadha. Galma olaanaa kan fidummoo itti fufiinsa qabaachuudha. Aadaa magariisummaa wayita gabbifannu kanatti namni hundi dammaqinaan fedhii keessaa maddeen akka hirmaatu hawwii kooti.

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru!
ግብርና ከኢትዮጵያ ዐበይት የኢኮኖሚ ምሦሦዎች አንዱ ነው። የአብዛኛው ሕዝብ ሕይወት ከግብርና ጋር በእጅጉ የተሣሠረ እንደ መሆኑ፣ የዘርፉ ውጤታማነት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ዛሬ ከክልል አመራሮች እና የግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የነበረን ውይይት እንዳረጋገጠልኝ፣ እንደ ስንዴ ላሉ እህሎች ያለውን ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የምንችልበት አቅም በእጃችን ነው። የውኃ ሀብታችንን በሚገባ በመጠቀም፣ የሰው ሀብታችንን በማብቃት እና የግብርና ዕውቀታችንን በማሳደግ፣ ያልለሙ መሬቶችን በማልማት እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ ተባብረን ከሠራን በአጭር ጊዜ ውስጥ ታላላቅ ስኬቶችን እናስመዘግባለን።

//

* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ባለፉት ጥቂት ወራት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በመያዝ አኩሪ ሥራ ተሠርቷል። ትናንት ከክልል አመራሮች ጋር በነበረን ውይይት፣ በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ ማስገባት እና ማዘዋወርን ለመግታት ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተነጋግረናል። ከእያንዳንዱ ምንጭ ወደ ሀገር የሚገባውን የመሣሪያ ዝውውር በአግባቡ ለመከታተል እና ሕገ ወጥ መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሁላችንንም ሥምሪት ይጠይቃል።

Ji'oota muraasa darbanitti namoota meeshaalee waraanaa seeraan ala daddabarsan hordofanii qabuudhaan hojii boonsaan hojjetameera. Marii kaleessa hooggantota naannolee waliin gooneen, meeshaalee waraanaa karaa seeraan alaa seenaniifi daddabarfaman dhaabsisuuf walta'iinsa cimsuun akka barbaachisu waldubbanneerra. Madda kamirraa iyyuu daddabarsa meeshaalee waraanaa gara biyyaatti seenu sirriitti hordofuufi daddabarsitoota meeshaalee seeraan alaa too'annoo jala oolchuuf hundi keenya bobba'uu barbaachisa

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
የኢትዮጵያ ዋና ዋና የእምነት ተቋማት በሰላም፣ በማኅበራዊ ደኅንነት፣ በሥነ ምግባርና በዘላቂ ልማት በጋራ ስለሚሠሩበት ሁኔታ ውይይት አድርገናል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትና ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር በስፋት ተነጋግረናል ።
በውይይቱ ላይ በእምነት ተቋማት መካከል አልፎ አልፎ የሚከሠቱትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል መንገድ ለመዘርጋት፣ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዐቅምን አቀናጅቶ ለመፍታት፣ ለአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ጠንካራ ተቋም በጋራ ለማቆም፣ በሕዝቦች መካከል መግባባትና አንድነት ለማምጣት ተቀናጅቶ ለመሥራት፣ ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎችን በትብብር ለማከናወን፣ እንዲሁም የትውልዱን ሥነ ምግባር በጋራ ለመቅረጽ ሐሳብ ተለዋውጠናል።

የእምነት ተቋማት ያላቸውን መዋቅር ፣ ተሰሚነት፣ የሰው ኃይልና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በጋራ ካቀናጁት የውጭ እጅ የምንጠብቅባቸውን ብዙ ችግሮች መቅረፍ እንደሚችሉ ገልጠዋል። ለዚህ ደግሞ ልዩነትን አክብሮ፣ የፖለቲካና የእምነት ድንበሮችን ጠብቆ፣ ነገር ግን ተጋግዞና ተናብቦ መሥራት ይገባል ሲሉ ሐሳብ ሰጥተዋል።

ከትናንት ይልቅ ዛሬና ነገ ላይ ማተኮር፣ ከግጭቶች ይልቅ በጋራ ዕሴቶቻችንና ዐቅሞቻችን ላይ መተባበር ኢትዮጵያ ዛሬ የምትፈልገው ነው። የእምነት ተቋማት በተቋም ምሥረታ ያላቸውን ልምድ በመጠቀም፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአደጋ ሥራ አመራር፣ በድህነት ቅነሳ፣ በርዳታና በሥነ ምግባር ግንባታ ላይ የሚያተኩሩ ጠንካራ ሀገራዊ ተቋማትን በጋራ ቢመሠርቱ፤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ እንደሚተርፉ እምነቴ ነው።


https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/