Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
158K subscribers
8.06K photos
375 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ኢትዮጵያ፡- አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የሚል ርዕስ ያለው የመጪዎቹ ዐሥር ዓመታት የልማት ዕቅድ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ የዕቅዱ ዓላማዎች ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት፣ ምርታማነት እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት፣ የሥርዓታት ለውጥ ማምጣት፣ የሴቶች እና የወጣቶችን ፍትሐዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ መሪነት ማረጋገጥ ናቸው፡፡

ሌሎች ዘርፎች ውጤታማ ዕድገት እንዲኖራቸው መሠረት የሚሆኑ አምስት ምሦሦዎችም ያሉት ይህ ዕቅድ፣ ያሉንን ጥንካሬዎች እና ዕምቅ ሀብቶች ጥቅም ላይ ለማዋል የታለመ ነው፡፡ በተለይም የኢነርጂ ዘርፍን የሚመለከተው ዕቅድ፣ ለአብዛኛዎቹ የልማት ፍላጎቶች እንዲሁም ለሁሉም ዘርፎች ኢነርጂ አስፈላጊ መሆኑን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡

የዐሥር ዓመት ዕቅዱ በውጤታማነት እንዲፈጸም የፌደራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት የሚከተሉትን ዐበይት ተግባራት መከወን ያስፈልጋቸዋል፡፡ 1. የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች እና ኢንቨስትመንቶች በሙሉ የነፍስ ወከፍ ገቢን ለማሳደግ አስተዋጽዖ እንዲኖራቸው ማስቻል፣ 2. ፕሮጀክቶች ጥራት እንዲኖራቸው በሚያስችል መልኩ ማንኛውም ወጪ በአግባቡ በጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣ እና 3. ‘ድህነትን ከመዋጋት’ ትርክት ወጥቶ ባለ ብዙ ገጽ ብልጽግናን ወደ መገንባት መሸጋገር፡፡

Karoorri misoomaa waggoota kurnan dhufanii kan mataduree 'Itoophiyaa: Fakkeenya Badhaadhinaa Afrikaa' jedhu qabu irratti ibsi dhiyaate......

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
የ #አረንጓዴዐሻራ ችግኞችን ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን ተክለናል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ አንድነት እንፈጥራለን!

Biqiltuuwwan #AshaaraaMagariisaa pirezdaantota naannolee waliin taa'uun dhaabneerra. Ashaaraa magariisaan tokkummaa uumuu ni dandeenya!
//

በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ
Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የሀገሬ ሕዝቦች፣
የተከበራችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማህበራትና የሀገር ሽማግሌዎች፣
ክቡራትና ክቡራን
ዛሬ ጠዋት ከኦሮሚያ፣ ከአማራ እና ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ጊዜ በበጎ ፈቃደኞች የሚካሄድ የክረምት የዜግነት አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ለወሊሶ ሊበን ትምህርት ቤት በሕዝብ ተሳትፎ የሚገነባን ሕንጻም እንዲሁ አስጀምሬያለሁ፡፡ በከተማዋ የሚካሄድ የአቅመ ደካሞችን ቤት የመገንባት ሥራ ላይም ለመሳተፍ ዕድል አግኝቻለሁ፡፡ ከርዕሰ መስተዳድሮች ጋር ችግኝ በመትከል #አረንጓዴ ዐሻራችንን አሳርፈናል፡፡

ያደጉ ሀገራት አሁን ያሉበት የዕድገት እና የብልጽግና ደረጃ ላይ የደረሱት በልፋት እና በድካም ነው፡፡ እኛም ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ በጎ ፈቃደኝነት ሌሎችን ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም ይጠቅማል፡፡ ከከተማ እስከ ክልል፣ ከክልል እስከ ሀገር በርትተን እየሠራን ኢትዮጵያችንን ለሁሉ ምቹ እናደርጋታለን!

Har'a ganama pirezdaantota naannolee Oromiyaa, Amaaraafi Somaalee waliin taanee tajaajilli lammummaa gannaa tola ooltotaan gaggeeffamu yeroo lammaffaaf Naannoo Oromiyaatti ifaan jalqabsiifneerra. Mana Barumsaa Walisoo Liibaniif gamoo hirmaannaa uummataatiin ijaaramus eegalchiiseera. Magaalattiitti hojii mana namoota humnisaanii dadhabaa ta'ee ijaaruu irrattis carraa hirmaachuu argadheera. Pirezdaantota kanneen waliinis biqiltuu dhaabuudhaan #AshaaraaMagariisa keenya keewwanneerra.....

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
#አረንጓዴዐሻራ በጉራጌ ዞን

#AshaaraaMagariisaa Godina Guraageetti


//
በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ
Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru!