Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
158K subscribers
8.06K photos
375 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ባለፉት ሶስት ዓመታት ከተካሄዱ ዐበይት ተቋማዊ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ እና ከፖለቲካዊ ግንኙነቶች ገለልተኛ የሆነ ብቁ አመራር እንዲኖረው መደረጉ ነው፡፡
ከክልል አመራሮች እና ከምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር ዛሬ ባካሄድነው ስብሰባ፣ እንደ መንግሥት በመጀመሪያው ዕቅድ መሠረት ለመቀጠል ፍላጎት እና ዝግጁነት ቢኖረንም፣ የምርጫ ቦርድ ለአጭር ጊዜ ምርጫውን ለማዘግየት ያቀረበው ሐሳብ ምክንያታዊ በመሆኑ በዚያው ተስማምተናል፡፡ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት በጉጉት የሚጠበቀውን እና ከተገመተው በተቃራኒ አያሌ መራጮች የተመዘገቡበትን 6ኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ እንዲቻል መንግሥት ምርጫ ቦርድን ለመደገፍ ባለው ቁርጠኝነት ይቀጥላል። ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የማካሄድ ባህል ባለመኖሩ፣ በዝግጅት ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ አንዳንድ ተግዳሮቶች አሉ። ነገር ግን ከቀደሙት ዓመታት በተሻለ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የተቻለንን ሁሉ በማድረግ፣ ወደፊት ለሚካሄዱ ምርጫዎች መሠረት እንደምንጥል ለመላው ኢትዮጵያዊያን አረጋግጣለሁ፡፡
የኢትዮጵያውያን ሕይወት ከዛፎች እና ከጫካ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው፡፡ ዛሬ የ2013ን የ #አረንጓዴዐሻራን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀምረናል። በ2011 የአካባቢን ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ አስበን የአራት ዓመት ዕቅድ በማውጣት ያቀረብነው ሀገራዊ ጥሪ አንድ አካል ነው፡፡ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የምግብ ዋስትናን ያለማረጋገጥ፣ አካባቢ ተኮር ግጭቶች እና የመሳሰሉ አሉታዊ ሁኔታዎችን የመከላከያ መንገዱ በእጃችን ነው፡፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” ብዬ ጥሪ አቀርባለሁ። ጥሪው ሀገራችንን አረንጓዴ እናልብስ፣ በክልል ፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ከመከፋፈል አልፈን፣ ለዚህ ታላቅ ሕዝብ በሚመጥን መልኩ፣ ኢትዮጵያችንን በብልጽግና እና በክብር በአንድነት የተፈጥሮ ልብሷን እናልብሳት ማለቴ ነው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኑ ኢትዮጵያን እናልብስ