Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
158K subscribers
8.06K photos
375 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
በሀገራዊ ጉዳዮች እና በቀጠና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና ከክልል አመራሮች ጋር የሚካሄድ የሁለት ቀናት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል። ስብሰባው መንግሥት በቀጣይ ሦስት ወራት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለመወያየት እና ዕቅድ ለማውጣት የታለመ ነው።

Two day meeting with Regional leadership has commenced today covering national and regional geopolitical issues with the aim of discussing and planning for activities to be undertaken as a government within the next three months.
ግብርና የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት እና #የኢትዮጵያብልጽግናራዕይ ማዕከል ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት ካሳካናቸው ግቦች ጥቂቶቹ፦

Agriculture is the backbone of our economy and central to our #VisionForProsperity. A few of the milestones we have achieved in the past three years:-
ባለፉት ሶስት ዓመታት ከተካሄዱ ዐበይት ተቋማዊ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ እና ከፖለቲካዊ ግንኙነቶች ገለልተኛ የሆነ ብቁ አመራር እንዲኖረው መደረጉ ነው፡፡
ከክልል አመራሮች እና ከምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር ዛሬ ባካሄድነው ስብሰባ፣ እንደ መንግሥት በመጀመሪያው ዕቅድ መሠረት ለመቀጠል ፍላጎት እና ዝግጁነት ቢኖረንም፣ የምርጫ ቦርድ ለአጭር ጊዜ ምርጫውን ለማዘግየት ያቀረበው ሐሳብ ምክንያታዊ በመሆኑ በዚያው ተስማምተናል፡፡ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት በጉጉት የሚጠበቀውን እና ከተገመተው በተቃራኒ አያሌ መራጮች የተመዘገቡበትን 6ኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ እንዲቻል መንግሥት ምርጫ ቦርድን ለመደገፍ ባለው ቁርጠኝነት ይቀጥላል። ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የማካሄድ ባህል ባለመኖሩ፣ በዝግጅት ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ አንዳንድ ተግዳሮቶች አሉ። ነገር ግን ከቀደሙት ዓመታት በተሻለ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የተቻለንን ሁሉ በማድረግ፣ ወደፊት ለሚካሄዱ ምርጫዎች መሠረት እንደምንጥል ለመላው ኢትዮጵያዊያን አረጋግጣለሁ፡፡