Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
158K subscribers
8.06K photos
374 videos
71 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
እስከ ዛሬ ግንቦት 9፣ 2012 ድረስ የተካሄዱ የምርመራ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ከ307‚000 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎችም 4.5 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ሁኔታዎች ያመላክታሉ፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ከተጠቁት ሀገራት ውስጥ አብዛኛዎቹ ያደጉ ሀገራት ናቸው፡፡ እነዚህ ሀገራት በፍጥነት ርምጃ ባለመውሰዳቸው እና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ባለማድረጋቸውን ይፀፀቱበታል፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ ቫይረሱን ለመመከት የሚያስችል ክትባት እስካሁን አልተገኘም፡፡ ስለዚህ፣ ቫይረሱን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ርምጃዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እጆችን ቶሎ ቶሎ በመታጠብ በንጽሕና መያዝ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልን በአግባቡ መጠቀም እና ሕዝቡ ለተወሰነ ጊዜ በቤት የሚቆይበትን ደንብ ተግባራዊ ማድረግን ይጨምራሉ፡፡

አካላዊ ርቀት እና በሙሉ ወይም በከፊል ሕዝቡ በቤት እንዲቆይ የማድረግ ርምጃ የቫይረሱ ሥርጭት በአስከፊ ሁኔታ ሳይባባስ ተግባራዊ ከተደረገ፣ ሀገራት የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት እና በጤና አገልግሎት ሥርዓት ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ ይችላሉ፡፡ ይህ ርምጃ ኢኮኖሚን እንደሚጎዳ ቢታወቅም፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ሥርጭቱን ለመቀልበስ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮቪድ19 ተጠቂ ከተገኘ ስምንተኛ ሳምንታችንን ይዘናል፡፡ እስካሁን 316 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም፣ ቀስ በቀስ እያሻቀበ ይገኛል፡፡

መንግሥት የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ፈጣን ርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ በተለይም የቫይረሱ በሀገራችን መገኘት በታወቀበት ሰሞን የሕዝቡ ምላሽ አዎንታዊና ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዳ ነበር፡፡ ቫይረሱ በአዝጋሚ ሁኔታ በመሠራጨቱ፣ ኢትዮጵያን ሊጎዳት እንደማይችል ማሰብ ተጀመረ። መሠረት የሌላቸው መላምቶችም እየተሠነዘሩ መጡ። ከዚህ የተነሣ፣ በርካታ ሰዎች የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ አካላዊ ርቀት መጠበቅንና እጆችን አዘውትሮ መታጠብን የመሰሉ ተግባራትን ቸል እንዲሉ አድርጓል፡፡ የአያሌ ዜጎቻቸው ሕይወት በቫይረሱ ከተቀጠፈባቸው፣ የጤና አገልግሎት ዘርፋቸው ከተናጋባቸው እና ኢኮኖሚያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ከተቃወሰባቸው ሀገራት ስሕተት ለመማር ካልቻልን የምንከፍለው ዋጋ እጅግ አስከፊ ነው፡፡

ስለዚህ፣ ኢትዮጵያውያን እና በኢትዮጵያ የምትገኙ ሁሉ ለአፍታም ሳትዘናጉ የወጡትን መመሪያዎች አጥብቃችሁ እንድትተገብሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

Bu'aan qorannoo hamma har'aatti, Caamsaa 9/2012, jiru akka mul'isutti weerarra dhukkuba COVID-19 n sadarkaa addunyaatti lubbuun namoota 307,000 olii darbeera. Nammoonni Vaayirasichaan qabaman immoo miliyoona 4.5 gahaniiru. Lakkoofsi kun kana caalaa dabaluu akka danda'u haalonni jiran ni mul'isu. Biyyootni garmalee Vaayirasichaan miidhaman irra caalaan isaanii biyyoota dinagdeen guddatanidha. Biyyoonni kunneen dafanii tarkaanfii fudhachuu dhabuufi tamsa'ina Vaayirasichaa dhaabuuf imaammata barbaachisu yeroon hojii irra oolchuu dadhabuu isaaniitti gaabbaa jiru. Kun nuuf barumsa guddaadha. Talaalliin Vaayirasicha ittisuuf dandeessisu hamma yoonaatti hin argamne. Kanaafuu tarkaanfiiwwan Vaayirasicha ittisuuf fudhachuu qabnu: gargar fageenya qaamaa eeguu, daddafanii harka dhiqachuufi qulqullinaan of eeguu, golgituu afaaniifi funyaanii sirriitti fayyadamuu, akkasumas uummanni yeroo murtaa'eef akka mana turu gochuu raawachuu barbaachisa.

Tarkaanfiin qaamaan gargar fagaachuufi uummanni guutummaatti yookaan gartokkeedhaan akka mana turu gochuu, utuu Vaayirasichi garmalee hin tamsa'iin yoo hojii irra oolfaman, biyyoonni tamsa'ina Vaayirasichaa ittisuufi dhiibbaa sirna tajaajila fayyaa irra gahu hir'isuuf ni danda'u. Tarkaanfiin kun dingdee akka miidhu beekamus hubaatii badaan utuu hin gahiin tamsa'inasaa dhaabuuf baay'ee barbaachisaadha. Itoophiyaatti edda namni jalqabaa Vaayirasichaan qabame argamee torban saddeet ta'eera. Hamma yoonaatti namoonni 316 Vaayirasichaan qabamaniiru. Biyyoota kanbiroo waliin yoo birqabaan ilaalamu lakkoofsichi gadi aanaa ta'us, suuta suuta ol ka'aa jira.

Mootummaan tamsa'ina dhukkubichaa ittisuuf tarkaanfiiwwan si'ataa fudhachaa tureera. Keessumaa tibba Vayirasichi biyya keenya seenuun isaa barame deebiin uummataa gaariifi Vayirasicha ittisuuf kan gargaaru ture. Vaayirasichi suuta jedhee tamsa'uu isaatiin Itoophiyaa miidhuu akka hin dandeenye yaaduutu jalqabame. Ta'innaan bu'ura dhugaa hin qabne dhagahamuu jalqaban. Kanarraa kan ka'e namoonni hedduun tarkaanfiiwwan akka qaamaan gargar fagaachuufi daddafanii harka dhiqachuu tamsa'ina Vaayirasichaa ittisuuf dandeessisan dagachuutti ka'ani. Dogoggora biyyoota lammiilee isaanii hedduu Vaayirasichaan dhabanii, sirni tajaajila fayyaa isaanii gaaga'ameefi dinagdeen isaanii garmalee miidhame irraa barchuu yoo dadhabne gatii baay'ee badaa ta'e nubaasisa. ........


https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ባለፈው ዓመት የ #አረንጓዴ ዐሻራ የተከላ ወቅት በሀገር ደረጃ የተተከሉት ችግኞች እንዲያድጉ በመላው ሀገሪቱ ያላሰለሰ የመንከባከብ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። ከእነዚህም መካከል፣ በአማካይ 84 በመቶ የሚሆኑት ጸድቀዋል። ለመጪው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምንዘጋጅበት በዚህ ወቅት፣ ጥረታችን ፍሬ ማፍራቱን መገንዘባችን ተስፋ ሰጪ ነው።

Bara darbe yeroo biqiltuu dhaabbii #AshaaraaMagarisa biqiltuuwwan guutummaa biyyaatti dhaabaman akka guddatan hojiin kunuusuu cimaan hojjetamaa ture. Isaan keessaas giddugalaan dhibbeentaan 84 qabataniiru. Wayita sagantaa biqiltuu dhaabuu bara dhufuutiif qophaa'aa jirru kanatti carraaqqiin keenya bu'a qabeessa ta'uu hubachuun abdii kan namatti horudha.
//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ውድ የሀገራችን ህዝቦች
ክቡራትና ክቡራን

‹‹ብዙዎቹ የፈጠራ ውጤቶች የፈተና ልጆች ናቸው›› ይባላል። የሰው ልጆች ከዛሬው ሥልጣኔያቸው ላይ የደረሱት በየዘመናቱ የተደቀኑባቸውን እንቅፋቶች ለማለፍ እውቀትና ክሎታቸውን በስፋት በመጠቀማቸው የተነሣ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። አንዳንድ ሊቃውንት ሲናገሩ ‹‹እኛ ሰዎችን ለዛሬው ክብር ያበቃን አዕምሮ ያለው ፍጡር በመሆናችን እና አዕምሯችንን እንድንጠቀም በሚያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፋችን ነው›› ይላሉ። እነዚህ ሁለቱ ባይኖሩ፣ ሁላችንም ከዛፍ ወደ ዛፍ ተንጠላጣይ ሆነን እንቀር እንደነበርም ይናገራሉ።

የሰው ልጆች አዳዲስ ጥበቦችን እንዲፈጥሩና ያሉትንም እንዲያሻሽሉ ከገፏቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በየዘመናቱ የሚከሰቱና የህልውና አደጋ የሚደቅኑ ወረርሽኞች ናቸው። እነዚህ ወረርሽኞች በሰዎች ላይ ካደረሱት መጠነ ሰፊ ጉዳት ባልተናነሰ ወረርሽኙን ለማሸነፍ ሰዎች የፈጠሯቸው ዘዴዎች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ልዩ ልዩ አሠራሮችና የአኗኗር ዘይቤዎች ተያይዘው ይጠቀሳሉ። ለችግር እጅ የማይሰጡ ሰዎች ፈተና ሲገጥማቸው ለመፍጠር ይገደዳሉ። የፈጠራን ፋና ከፈነጠቀው እሳት አንስቶ እስከ ዘመናችን ውስብስብ ኮምፒውተሮች የተፈጠሩት ፈተናዎች ይዘውት የመጡትን እርግማን ትተው ወደ በረከት በሚቀይሩ ጎበዞች ነው።

ኖህ መርከቢቱን ለመስራት የተነሳው ከሚመጣው የጥፋት ውሃ ህዝብን ለማዳን በሚል ነበር፤ ዛሬ መርከብ ለእቃ ማጓጓዣነትና ለመዝናኛነት ይውላል። መከራና ችግር አንዳንድ ደካሞችን አንኮታኩቷቸው ሲያልፍ፣ አንዳንድ አሳቢዎችን ደግሞ ይበልጥ ያጠነክራቸዋል። ያ ጥንካሬያቸውም መልሶ ህዝብን የሚጠቅም ይሆናል። ካወቅንበት ፈጠራ የማሰብና ችግርን ወደ እድል ለመለወጥ የሚደረግ ጥረት እንጂ ሌላ ተአምር እንዳልሆነ እኛ የሰው ልጆች ከታሪካችን በሚገባ ልንማር እንችላለን።

ከዚህ ዘመን በፊት ሲከሰቱ የነበሩ ወረርሽኞች ገሚሶቹ በክትባት የተቀሩትም በህክምና ለመዳን ከመብቃታቸው በፊት የብዙዎችን ህይወት ቀጥፈዋል። ያም ሆኖ የፈጠራ ሰዎች ጭንቅላታቸውን ተጠቅመው ለበሽታዎቹ መድሀኒትና ክትባት ከመስራት ባለፈ ወደፊት ለሚገጥሙን ችግሮች መፍትሔ የምንሰጥበትን ፍጥነት እንድንጨምር የሚያስችለንን በዘመናት የተከማቸ እውቀትና እምቅ አቅማችንን እንድናሳድግ አስችሎናል። ዛሬም የተጋረጠብንን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለማለፍ እጅግ የተሻለው መንገድ አንጡራ ሀብታችንንና ዕምቅ ዐቅማችንን ከአዳዲስ ፈጠራዎቻችን ጋር አቀናጅተን መጠቀም ነው። አንጡራ ሀብት የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ያገኘው የሚታይና የማይታይ ሀብት ሲሆን፣ ዕምቅ ዐቅም ደግሞ የሰው ልጅ ያለው አእምሯዊ አቅም ማለት ነው። ይህ አእምሯዊ አቅም የበለጠ በተፈተነ ቁጥር የበለጠ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል እየሆነ ይመጣል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከኮቪድ በኋላ እጅግ የተሻለችና ፈተናውን በድል ያለፈች ሀገር ለማየት ከፈለግን እነዚህ ሦስቱን አቅሞቻችንን አጣምረን መጠቀም የግድ ይለናል። እያንዳንዷን ሀብት በሚገባ መፈተሽና ያለ ብክነት መጠቀም አለብን። ሀብትን የሚያበዛው የተገኘው መጠን ብቻ ሳይሆን የአጠቃቀም ችሎታውም እንደሆነ ግልጽ ነው። በተመሳሳይ ያለንን ሀብት በተገቢው ጊዜ፣ ለተገቢው ዓላማ፣ በተገቢው መንገድ መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ሲሆን እንደ ሀገር ሀብትን መልሶ ጥቅም ላይ የማወል አቅምና ጥበብን በየጊዜው ማሳደግ ተገቢነቱ አያጠያይቅም። ለዚህም ሕብረተሰባችንን በማስተማርና ንቃተ ህሊናው እንዲዳብር በመትጋት በኩል ሁላችንም ሀላፊነት አለብን። ትልቁ የሰው ልጆች የሀብት ምንጭ አዕምሮ እንደመሆኑ መጠን፣ እውቀት ላይ የተመሰረቱ ሀብቶቻችንን አብዝተን ለመጠቀም ከፍተኛ ትግል ከማድረግ መቦዘን የለብንም።
የማይነጥፈውን የሀብት ምንጭ አዕምሮን ወደ ሀብትነት የምንቀይርበት ዋነኛው መንገድም ፈጠራ ነው። ፈጠራዎች ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና በርካሽ ዋጋ ለብዙዎች ተደራሽ መሆን ሲችሉ ሀገር ከፈጠራዎቹ የምታገኘው ጥቅም በጣም ከፍተኛ ይሆናል። ለዚህም፣ ደግሞ ደጋግሞ ማሰብ በእጅጉ ይጠይቃል። ነገሮችን በተለያዩ አቅጣዎች መመልከት፣ እንደ አዲስ መፈተሽ እና ሳይታክቱ መሞከር የፈጠራ ቁልፎች ናቸው።

ኮቪድ 19`ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል። በዚህ መንገድ ፋታ የማይሰጠውን ወረርሽኝ ፋታ ልንነሣው እንችላለን። በአሁኑ ወቅት፥ በገጠርና በከተማ የሚገኙ ለእርሻ ምቹ የሆኑ መሬቶቻችንን ለምግብ ሰብል ምርት ማዋል አለብን፤ አምራች ኢንዱስትሪውና ሠራተኞቹ ዐቅማቸውን ሁሉ ለተጨማሪ ምርት እንዲያውሉ ማበርታት ይገባናል፤ በግብርና ሥራ ላይ የተሠማሩ አርሶ አደሮችና ባለሞያዎችን ማበረታታት ተገቢ ነው፤ በመጭው ክረምት ያቀድነውን የ5 ቢልዮን ችግኝ ተከላ ወገባችንን አሥረን ማሳካትም ይኖርብናል። በተጨማሪም ዜጎች በቤት ሲቀመጡ ሊያከናውኗቸው የሚገቡ የሞያና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከማትጋት በዘለለ የሀገር ፍቅርና የሕዝቦች አንድነትን ማጠናከር አለብን።

በዚህ መልኩ ለወረርሽኙ ስርጭት እድል ሳንፈጥር ለሀገር ግንባታ ከተጋን ያለ ጥርጥር ኮሮናም በቀላሉ ይሸነፋል፤ ሀገራችንም በብልጽግና ጎዳና ትረማመዳለች። ለዚህ ደግሞ የቴክኖሎጂና የኪነ ጥበብ ፈጠራዎች የበለጠ ጉልበት እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። የማኅበረሰቡን አስተሳሰብ የሚያሳድጉና ፈተናን ወደ ዕድል የሚቀይሩ አብሪ ሐሳቦች በተለይ በዚህ ወቅት በእጅጉ ያስፈልጉናል።

ስለሆነም መንግስት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የሕዝቡን ኖሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂና የኪነ ጥበብ ፈጠራ ያሏቸውን ኢትዮጵያውያን ማበረታታት ይሻል። ከዚህ አኳያ፡-
• የገበሬውን ምርታማነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ አዳዲስ አሰራርና ቴክኖሎጂዎች፤
• የከተማ ግብርናን የሚያበረታቱ፣ የሚያሳልጡና ውጤታማ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ዘዴዎች፤
• የፋብሪካ ምርታማንትን የሚያሳድጉ የተመረጡ መንገዶችና አሰራሮች፤
• ዜጎቻችን በቤት ውስጥ ሲቀመጡ የንባብ ፍላጎታቸውና ችሎታቸው እንዲዳብር የሚያደርጉ ፈጠራዎች፤
• በቤት የሚቀመጡ አረጋውያን፣ ጎልማሶች፣ ወጣቶችና ሕጻናት በቀላሉና ወደዋቸው ሊያከናውኗቸው የሚችሉ ማራኪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፤
• ሕዝቡን ለፈጠራ፣ ለአዳዲስ ሙከራዎች እና የቴክኒክ እውቀቱን ከፍ ለማድረግ የሚረዱ ድርሰቶች፣ ሙዚቃዎች፣ ሥዕሎች፣ አጫጭር ድራማዎችና አጫጭር ፊልሞች፤ እንዲሁም
• የሕዝቦቻችንን አንድነት፣ የእርስ በርስ ትውውቅና የሀገር ፍቅር ስሜት የሚያሳድጉ ጥበቦችና ፈጠራዎች ያሏችሁ ሳትዘገዩ አሁኑኑ አውጧቸው።

በዚህ መልኩ እስከ መስከረም ድረስ በተለያዩ ሚዲያዎችና መድረኮች የሚቀርቡ የተሻሉ የፈጠራ ውጤቶችን መርጦ በቀጣዩ ዓመት ለመሸለም በመንግስት በኩል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው። ስለሆነም ፈጠራዎቻችሁን ያለማቋረጥ በተለያዩ መንገዶች ለሕዝብ አቅርቧቸው። ሥራዎቻችሁን በዋነኞቹና በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የማስተዋወቂያው ትክክለኛ ጊዜ አሁን ነው። ይሄን ተከታትሎ የሚይዝ፣ ከየሚዲያው ወስዶ የሚመዘግብና ለሽልማት የሚያጭ አካል መንግሥት በቅርቡ አቋቁሞ የሚያሳውቅ ይሆናል።

አመሰግናለሁ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!


https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
እንኳን ለ2012 የሲዳማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ።

የሲዳማ ፊቼ ጨምበላላ የአዲስ ዓመት በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ በቅርስንት ከተመዘገቡት አምስት የሀገራችን ቅርሶች መካከል ነው። ኢትዮጵያ ባህለ ብዙ፣ ዕሴተ ብዙ፣ ጸጋ ብዙ፣ መሆኗን ከሚያሳዩ ህያው ምስክሮች አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተስፋ የተሞላ፣ አዲስን ነገር አበክሮ የሚሻ መሆኑን እንደ ፊቼ ጨምበላላ ያሉ አዲስን ዓመት በተስፋና በጉጉት የመጠበቂያ በዓላት በሚገባ ያመለክቱናል፡፡

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከሥነ ፈለክ ጋር የነበረንን ጥንታዊ የዕውቀት ግንኙነት ያመለክተናል፡፡ ሽማግሌዎቹ የበዓሉን ዕለት የሚወስኑት የመሬትን፣ የፀሐይን፣ የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓተ ዑደት በመመልከትና የእነዚህን አካላት ቅንጅት በማጥናት ነው፡፡
ፊቼ ጨምበላላ በዓል ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ስላሸጋገረን ምስጋና፣ መጪው ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና እንዲያደርግልን ምልጃ፣ ለፈጣሪ የሚቀርብበት በዓል ነው፡፡ የተጣሉ ዕርቅ ያወርዱበታል፤ ፈጣሪ ለሽማግሌዎች የሰጣቸው እውነት ወይም ሃላሌ ይጸናበታል፤ ሕፃናትና ከብቶች ጠግበው ይዉሉበታል።

በፊቼ ጨምበላላ ጊዜ ሽማግሌዎቹ የሚሰጡት ምክር ሰባት እጅግ ወሳኝ በሆኑ ዕሴቶች ላይ የተመሠረ ነው፡፡ ሕዝቡ ጠንክሮ እንዲሠራ፣ አረጋውያንን እንዲያከብርና እንዲረዳ፣ ሀገር በቀል ዛፎችን እንዳይቆርጥ፣ እንዲከባከብ፤ ሰዎች ከስንፍና እንዲርቁ፣ ልመናን እንዲጸየፉ፣ ከስርቆትና በሐሰት ከመመስከር እንዲቆጠቡ ይመክራሉ፡፡ በዓሉ በዋናነት ተካፍሎ መኖርን ያስተምራል፡፡ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ይጠይቃል፡፡ ማኅበራዊ ትብብርን ያጠናክራል፡፡ በሰላም አብሮ መኖርንና ከሌሎች ጋር መተሣሠርን ያበረታታል፡፡

ከሁሉም በላይ ፊቼ ጨምበላላ ለሕጻናትና ለዕውቀት ሽግግር የላቀ ሥፍራ አለው፡፡ ልጆች የእናት አባቶቻቸው ታሪክና የሕዝቡ ባህል ይነገራቸዋል፡፡ በቃል እየተላለፈ የመጣውን ትውፊት ይወርሳሉ፡፡ በበዓል ቀን በሚደረገው ክዋኔ እንዲሳተፉና ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይደረጋል፡፡ ነባሩ ዕውቀት ከወላጅ ወደ ልጅ በሽማግሌዎች ትረካ የሚተላለፈው በዋናነት በፊቼ ጨምበላላ ወቅት ነው፡፡ ይህ መቼም ቢሆን በየቤታችን ልንተገብረው የሚገባ ድንቅ ዕሴት ነው፡፡

ሲዳማዎች ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ ተምሳሌት በሆነው በ "በ" ቅርፅ በሚሠራው "ሁሉቃ" ልጆቻቸውንና ከብቶቻቸውን በማሳለፍ፣ በአሮጌው ዓመት የነበሩ ችግሮች፣ መከራዎች፣ በሽታዎች ከኋላችን ቀርተው፣ አዲስ ወደ ሆነውና ብሩህ ተስፋ ወደሚታይበት የብልጽግና ጎዳና እኛንም ምራን በማለት ይለምናሉ፡፡ ለዚሁ ዕለት ተብሎ ወደሚዘጋጀው ለምለም መስክ ከብቶቻቸውን ያሠማራሉ። እኛም ዓለማችንን እና ሀገራችንን ሥጋት ላይ የጣለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ፈጣሪ ከኋላችን አስቀርቶ፣ በአዲሱ ዓመት ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲመራን ከሲዳማዎች ጋር አብረን ፈጣሪን እንማጸናለን፡፡

የዘንድሮውን የፊቼ ጨምበላላ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ሁላችንም ስንጓጓ ነበር። ይሁን እንጂ በኮሮና ቫይረስ ምከንያት እንደዚህ ቀደሙ በጉዱማሌ ሕዝብ በተሰበሰቡበት ለማክበር የሚቻል አልሆነም። የሲዳማ ሽምግሌዎች ዓለማችን ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት በዓሉ በቤት እንዲከበር ያስተላለፉት ወቅታዊ መልእክት ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ኃላፊነት የሚሰማቸው፤ ከምንም ነገር በላይ የሰው ሕይወት የሚገዳቸው መሆኑን ያሳየ በመሆኑ አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ።

የሲዳማ የባህል አባቶች እና ሽማግሌዎች ያስተላለፉትን መመሪያ በማክበር፣ ሁላችንም በየቤታችን በመሆን፣ እጆቻችንን እየታጠብን፣ ርቀታችንን ጠብቀን፣ ሌሎችንም እየረዳን፣ የዘንድሮን የፊቼ ጨምበላላ በዓል እናከብራለን። የፈጣሪ በጎ ፍቃዱ ሆኖ፣ ይህንን ወረርሽኝ አሸንፈን ለከርሞ እንደከዚህ ቀደሙ፣ በአደባባይ በጉዱማሌ ከመላው ሲዳማ ጋር ለማክበር ፈጣሪ ይርዳን።

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ከሳምንታት በፊት የተደረገው 'ማዕድ እናጋራ' የሚለውን ጥሪ ሰምተው ምግብ ብቻ ሳይሆን በቀን ሥራ የሚተዳደሩና በ በ#COVID19 ምክንያት ተፅእኖ የደረሰባቸው እስከ 100 ለሚደርሱ ግለሰቦች መጠለያ የሚሰጡ የሁለት ወንድማማቾችን መልካም ሥራ ስሰማ በጣም ተደስቻለሁ ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ራሳቸው የቤት ባለቤቶች ሳይሆኑ ተከራይተው የሚኖሩበትን ቤትና ምግባቸውን ከማካፈል በተጨማሪ ሕይወታቸውን ለችግረኞች ከፍተዋል ፡፡ የእነሱ እንቅስቃሴ በእውነቱ ልብን በፍስሐ የሚሞላ ነው። እናም ሁለቱ ወንድማማቾች እና ሌሎችም ገሐድ ሳይወጡ ደግነትና እና መልካም ሥራ የየዕለት ተግባራቸው የሆነ ግለሰቦች መኖረ ኅብረተሰባችንን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ሙጫ ነው፡፡ እኛ የእያንዳንዳችን ጠባቂዎች ነን!


Waamicha 'Soorata Walii Qooduu' torbeewwan muraasa dura darbeef deebii kennuudhaan obbolaan lama soorata qofaa utuu hin ta'iin namoota 100 ta'an hojii humnaatiin jiraataniifi sabab #COVID-19n jiruun isaanii midhameef bakka jiraatan qopheessuu isaanii dhagahee baay'ee keessi koo tuqame. Obbolaan kunneen manichi utuu kan isaaniillee hin ta'iin mana kireeffatan keessatti balabala isaanii fi jireenya isanii warra rakkataniif bananii soorataafi mana isaanii qoodaniiruufi. Gochi isaanii dhugumaan kan garaa nama qabbaneessudha. ......

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን ለመደገፍ አብረው መሰብሰባቸው የሚደነቅ ብቻም ሳይሆን ብሄራዊ አገልግሎትም ነው፡፡ ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር 11.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግል መከላከያ መሳሪያዎችን ፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን እና ሌሎች አቅርቦቶችን ስላበረከቱ አድናቆቴን መግለፅ እወዳለሁ ፡፡

Itoophiyaanonni lammii isaanii Itoophiyaa deeggaruuf walgahuun dinqisiisaa qofa utuu hin ta'iin gocha tajaajila biyyaalessati. Dhaabbanni Walta'iinsa Idiladdunyaa Mirgoota Itoohiyaanotaatiif, Itoophiyaanota biyya alaa jiraatan qindeessuudhaan meeshaalee dhuunfaa tuttuqaa ittisan, haguugduu fuulaafi kanbiroo birrii miliyoona 11.5 baasan arjoomuu isaatiif dinqisifannaa koo ibsuufiin barbaada.

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *
* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ኢትዮጵያ ኮቪድ19ን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ፣ የመመርመሪያ ኪቶችን የላኩልንን የቴንሴንት ፋውንዴሽኑን ማ ሁዋንቴንግን አመሰግናለሁ። እንዲህ ያሉት የአጋርነት ሥራዎች፣ ኢትዮጵያ ቫይረሱን የመመርመር አቅሟን እንድታጠናክር የሚያግዙ ናቸው።

Faawondeeshiniin Ma Huwanteengi Tensent kiitota qorannaa dhiyeessuudhaan tattaaffi #Itoophiyaan #COVID-19 ittisuuf gootu deeggaruu keessaniif isinin galateeffadha. Hojiin michoomaa akkasii Itoophiyaan humna qorachuu ishee akka bal'iftuuf murteessaadha.
//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ከወንድሜ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር በኢንተርኔት ውይይት አካሂደናል። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትርም በውይይቱ ተሳትፈዋል። ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ለሁሉም አካላት በሚስማማ መፍትሔ ላይ መክረናል። የተሳሳተ ግንዛቤ የነበረባቸውን ጉዳዮች አጥርተን ተነጋግረናል። በውኃ ሚኒስትሮቻችን አማካኝነት የቴክኒክ ውይይቶችን ለመቀጠል እና ያልተቋጩ ጉዳዮችን አጠናቅቀን ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለመቀየስ ተስማምተናል። የሕዳሴው ግድብ ለሁሉም ሀገራት የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዳለው እና በመተባበር ዕድሉን ልንጠቀምበት እንደሚያስፈልግ በአጽንዖት አስረድቻለሁ።

Obboleessa koo Ministira Muummee Abdallaa Hamdook waliin intarneetiidhaan marii'anneerra. Ministiroonni Dhimma Alaafi Bishaaniifi Inarjii Itoophiyaas maricha irratti hirmaataniiru. Hidha Haaromsaa ilaalchisee furmaata qaama hundumaaf tolu irratti walmarii'anneerra. Dhimmoota hubannoo dogoggoraa turan irrattis waliigalchinee dubbanneerra. Karaa ministiroota bishaanii keenyaan marii teekniikaa itti fufuufi dhimmoota hin xumuramne xumurree haala itti hundumtuu fayyadamaa ta'u faluuf waliigalleerra......


https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
በኮቪድ19 ወቅት፣ የፈጠራ ሥራን ለመሥራት የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው፣ ብዙዎች ጠቃሚ ሐሳቦችን እያፈለቁ ይገኛሉ። ቀደም ብሎ በነበረን ውይይት፣ ጃክ ማ ተጽዕኖ አሳዳሪ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችን ለመደገፍ ታስቦ ስለ ተዘጋጀው የአፍሪካን የቢዝነስ ጀግኖች ( www.africabusinessheroes.org/en/ ) ነግረውኛል። በፈጠራ ሥራ የተሠማራችሁ ኢትዮጵያውያን በመሉ የድረ ገጹን መረጃ አንብባችሁ በማመልከት፣ በቀጣና ደረጃ የውድድሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ አበረታታለሁ።

Yeroo #COVID -19 kanatti hojii kalaqaa jajjabeessuuf waamicha taasifamee tureef deebii kennuudhaan, namoonni hedduun yaadota fayyadan burqisiisaa jiru. Maree duraan tureen karaa Jack Ma namoota abbaa kalaqaa dhiibbaa uuman deeggaruuf yaadamee gootota biznasii Afrikaa ( www.africabusinessheroes.org/en/ ) qophaa'eera. Itoophiyaanonni hojii kalaquu irratt bobbaatan odeeffanno marsariitichaa dubbisuudhaan hirmaattanii akka naannootti akka dorgomtan isinan jajjabeessa.

* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/